Friday, February 10, 2012

ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያኔን አስጠብቃለሁ፣ ለሥርዓቷ የማይገዙትን እቃወማለሁ

በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሆነው እንደልጅ ተወልደው ጡቷን ጠብተው፣ ዳቤዋን በልተው፣ ከክብር ቦታ ደርሰው ሥርዓቷን ወደጎን ብለው፣ይልቁንም በሃይማኖት ከማይመስሉን ጋር በማበር ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችንን ለውርደት፣ ልጆቿን ለስደት የዳረጉትን የቤተ ክርስቲያን አባት መሰሎችን፣ ነገር ግን አሳዳጆችን፥ ልጅ መስለው ነገር ግን በውስጧ ምንፍቅና የሚዘሩን፥ በአጠቃላይ ለሥርዓቷ የማይገዙትን ከቅዱስ ሲኖዶስ አባላት ጀምሮ እታች እስካሉት ለሥርዓቷ ግድ የሌላቸውን፣ ይልቁንም የግል ሃብታቸውን እና እውቅናቸውን ለማትረፍ ቀን ከሌሊት ደፋ ቀና የሚሉትን እኛን መስለው ሊነጥቁን የተነሱብንን አጥብቄ እቃወማቸዋለሁ፣ ለሥርዓቷም መከበር የበኩሌን አደርጋለሁ፣ እወነቱን በመመስከር፣ ቤተ ከርስቲያንን ከሚያውኩት ጋር ባለመተባበር፣ ለሥርዓቷ የማይገዙትን በመቃወም፣ ተው በማለት እረዳለሁ። ለዚህም የቅዱሳን አምላክ ይርዳን አሜን።

አጥብቀን ልንታገለው የሚገባን እውነታ!

ዛሬ ለሥርዓተ ቤተ ክርስትያን ግድ የሌላቸው ለግል ከርሳቸው እና ጥቅማቸው የሚሯሯጡ አባቶች ተብዬዎች፣ የጥንት አባቶቻችን የሰሩልንን ቀኖና ወደጎን በመተው ያለ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ብዙ ሥራዎችን እየሰሩ ያሉ ሰዎች እኛ ውስጥ ሆነው የኛ የሆነውን ለጠላት እየሰጡ ያሉበት ጊዜ ላይ ደርሰናል።
ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ወልዳ መካን፣ አሳድጋ ለመናፍቃን እረዳት የሆኑበት ከመቼውም ጊዜ በላይ ትልቅ ችግር ውስጥ ያለችበት ጊዜ አሁን ነው፣ ስለዚህ እያንዳንዱ የተዋሕሶ ልጆች በሙሉ በአርባና በሰማኒያ ቀን ከአብራከ መንፈስ ቅዱስ የተወለድን ሁላችን በአንድነት ልንነቃ እና ልንጠብቅ የሚገባን ጊዜ አሁን ነው። ሰዎቹ በአሁን ሰዓት በትልቅ ቤተክርስቲያንን የማፍረስ ሥራ ላይ ተሰማርተው ይገኛሉ፡ ለምሳሌ በዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ "የቤተ ክርስቲያን የውጪ ግንኙነት" በሚል የተከፈተ ጽህፈት ቤት አለ፣ ይህ ጽህፈት ቤት በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ልዩ ፊርማ ተፈቅዶ የተከፈተ ጽህፈት ቤት ነው፣ ነገር ግን የቅዱስ ሲኖዶስ ወይም የቋሚው ሲኖዶስ እውቅና የለውም ለዚህም ሥራ ሊሠሩ (ሊያስፈጽሙ) የተላኩት ሦስት ግለሰቦች በሃገሩ ነዋሪዎች ናቸው፣ ሕዝቡን ያውቁታል፣ ህጉን ኖረውበታል፣ በቀላሉ ሰዎች ሊቀበሏቸው ይችላሉ ተብለው የመጡ እና ሥራውን በመሥራት ላይ ያሉት ግለሰቦች የሚከተሉት ናቸው

፩ኛ/ አቡነ ፋኑኤል
፪ኛ/ አባ ሰረቀ ወልደ ሳሙኤል
፫ኛ/ ዲ/ን ኃይለ ጊዮርጊስ ጥላሁን (ከድቁናው የተሻረ)

እነዚህ ግለሰቦች ገለልተኞችን እናቀራርባለን፣ የራቁትን እናቀርባለን፣ የቤተ ክርስቲያን አንድነትን እናመጣለን በሚል ሽፋን ዛሬ ሌት ተቀን ደፋ ቀና እያሉ ይገኛሉ፥ በጣም የሚያሳዝነው ለዚህ ጽህፈት ቤት ሙሉ የሠራተኛ ደሞዝ (ሦስት ደሞዝተኞች)፣ የጽህፈት ቤት ኪራይ፣ ለጽህፈት ቤቱ የሚያስፈልገውን ማንኛውንም ሎጂስቲክ ቁሳቁስ በአጠቃላይ ወጪዎቹ ሁሉ የሚሸፈኑት በዓለም አብያተ ክርስቲያን ጽ/ቤት ነው (ሚኖናይት፣ አድቬንቲስት፣ ፕሪንስተን ቲዎሎጂ ሴሚናሪ፣ በአጠቃላይ ፕሮቴስታንቶች) የሚደግፉት ጽ/ቤት ነው።
ሌላው ለጆሮ ጭው የሚያደርገው የጽ/ቤቱ የበላይ ተጠሪ ተብየው የቀድሞው ዲያቆን ያአሁኑ አቶ ኃይለ ጊዮርጊስ ነው፣ መረጃው በእጃችን ባይገባም እንደሰማነው በአሜሪካ ውስጥ ላሉት ሦስቱም ሃገረ ስብከት ሊቃነ ጳጳሳት ደብዳቤ በመፃፍ እርሱ በቅዱስ ፓትሪያሪኩ ተሹሞ ከመጣ ጀምሮ ሦስቱም ሊቃነ ጳጳሳት ተጠሪነታቸው ለዚሁ አቶ መሆኑን ከማስፈራሪያ ጋር እንደደረሳቸው ይነገራል።
እንዲህ ስርዓት ሲፈርስ፣ ያለህጓ የመጡበት የማይታወቁ ሰዎች መጥተው የአባቶቻንን ሥርዓት ሲያፈርሱ፣ ህጓን ሲፃረሩ፣ ለሌላ ሃይማኖት ሊሰጡን ደፋ ቀና ሲሉ ዝም ብሎ ማየት በታሪክም ያስወቅሳል፣ መጪውስ ትውልድ ምን ይላል።
ስደተኛው ሲኖዶስ ብለው ሲነሱ፣ ተው አይሆንም ሲኖዶስ አይሰደድም ስንል፥ ዛሬ ደግሞ በአንድ መንበር ሥር በሚያገለግሉ ነገር...

Thursday, February 9, 2012

በእንተ-መጋቢሃ ለዛቲ ገጽ

ብት--ፈርጡን--በቤትም በጉባኤም፣ በመሥመርም አፍኣ-መስመርም፤ በተገኘው ቦታ ኹሉ፤ ለማየት እና ለማሳየት በጥረት ላይ ያለ አንድ ታናሽ ደቅ (የግእዝ አሽከር)፤ የመኖሪያ ቀያቸው ባገርቤትም ቢሉ በውጭ አገር ኾኖ፤ ነገር ግን ለትምርት፣ ለሥራ ወይ ለሽርሽር በ"ሳይበር-አገር" የሚመላለሱ የኢትዮጵያ ልጆች እና ወዳጆች፣ መርበብቱን ተጠቅመው ግእዝን እና የግእዝን ሥነ-ጽሑፍ ከትርጓሜው ስልት ጋራ ይማሩባት ዘንድ ይችን ት/ቤት ተከለ። በተማሪ ዐቅሙ።